ምህረቱ ገብሬ (ኢንጂነር)
በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ ኃላፊ
መልዕክት
ሀዋሳ ከተማ የተመሠረተችበትን ዓመት ከሌሎች የሀገራችን ከተሞች ጋር በንፅፅር ሲታይ ወጣት ነች ቢያስብልም በቀደምት ስርዓቶች በነበሩ የተዛቡና የተሳሳቱ አመለካከቶችና አሰራሮች የተነሳ ከተማዋ ካላት የለውጥ ምቹነት አንጻር አበረታች ለውጦች ተመዝገበዋል ብሎ መናገር ይቻላል። በዚህ ረገድ የከተማዋ ዋነኛ ተልእኮ በአካባቢው የሚኖረውን ሰብአዊና ተፈጥሮአዊ ሀብት (የሰው ኃይል፣ ቴክኖሎጂ፣ መሬት፣ ውሃ፣ ማዕድን፣ ..ወዘተ) ከመንግስት የሚገኘው ውስን በጀት አቀናጅቶ በመምራትና ጥቅም ላይ በማዋል ጥራትና ደረጃቸውን የጠበቁ የመሠረተ ልማት አውታሮች በመዘርጋት እና ከተቋሙ የሚጠበቁ አገልግሎቶችን በቅልጥፍና በጥራት በመስጠት ውብ፣ ፅዱና ለመኖሪያ ምቹ፣ ለኢንቨስትመንትና ለቱሪዝም ተመራጭ የሆነ ከተማ ማድረግ ነው፡፡
በዚህም ህዝቡን በማህበራዊና አኮኖሚ ልማት ሙሉ ተሳታፊና ተጠቃሚ ሊያደርጉ በሚያስችሉ ዋና ዋና ሥራዎች ትኩረት በማድረግ ሠፊ ርብርብ ተደርጎ ብዙ ሰው-ተኮር ለውጦች መጥተዋል፡፡ ልማቱና የሥራ ዕድል ፈጠራው አካታችና ዘላቂነት ያለው የከተማ ፕላንና ልማት፤ አዋጭነት፣ ግልፅነትና ተጠያቂነት ያለው የመሬት አቅርቦትና ማኔጅመንት፤ ሕብረተሰቡንና የግል ዘርፉን ያሳተፈ የቤት ልማትና አቅርቦት፤ በጥራት፣ በተመጣጣኝ ወጪና ወቅቱን የሚመጥኑ አበረታች ለውጥ ማስመዝገብ ተችሏል።
ይህም እንደ ከተማ በተወዳዳሪነት የሚሠራ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪና ማኔጅመንት አሰራርና የማስፈፀም አቅም በመገንባት የመልካም አስተዳደር መርሆዎችን ተከትሎ የተከናወና ነው፡፡ የሀዋሳ ከተማ ልዩ ሚናዋን በመለየት የኢንዱስትሪ፣ የገበያና የአገልግሎት ማዕከልነተዋን በአግባቡ ለመወጠት የሚያስችል ከአካባቢ ከተሞች እንዲሁም ገጠር ጋር በማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ካባቢያዊ ጉዳዮችን መስተጋብር በመፍጠር ተመጋጋቢና የተቀናጁ ሆነው እንዲለሙ የሚስችል እንዲሆን የተሰራ በመሆኑ ዘርፋ ብዙ ስኬቶች ማስመዝገብ ተችሏል፡፡
Mission

Vission

Values

Services
Recent News
የካቲት 3/2016
“ፖሊዮን ጨርሰን እናጥፋ” በሚል መሪ ሐሳብ የ2016 ሐዋሳ ሐይቅ ግማሽ ማራቶን ውድድር ለ12ኛ ጊዜ ተካሂዷል።
ውድድሩን የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ አቶ መኩሪያ ማርሻዬ በክብር እንግነት በመገኘት አስጀምረዋል።
በስድስት የውድድር ዘርፎች 150 አትሌቶችን ጨምሮ ከ4 ሺህ በላይ የማኅበረሰብ ክፍሎች በውድድሩ ተሳትፈዋል…