ምህረቱ ገብሬ (ኢንጂነር)
በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ ኃላፊ
መልዕክት
ሀዋሳ ከተማ የተመሠረተችበትን ዓመት ከሌሎች የሀገራችን ከተሞች ጋር በንፅፅር ሲታይ ወጣት ነች ቢያስብልም በቀደምት ስርዓቶች በነበሩ የተዛቡና የተሳሳቱ አመለካከቶችና አሰራሮች የተነሳ ከተማዋ ካላት የለውጥ ምቹነት አንጻር አበረታች ለውጦች ተመዝገበዋል ብሎ መናገር ይቻላል። በዚህ ረገድ የከተማዋ ዋነኛ ተልእኮ በአካባቢው የሚኖረውን ሰብአዊና ተፈጥሮአዊ ሀብት (የሰው ኃይል፣ ቴክኖሎጂ፣ መሬት፣ ውሃ፣ ማዕድን፣ ..ወዘተ) ከመንግስት የሚገኘው ውስን በጀት አቀናጅቶ በመምራትና ጥቅም ላይ በማዋል ጥራትና ደረጃቸውን የጠበቁ የመሠረተ ልማት አውታሮች በመዘርጋት እና ከተቋሙ የሚጠበቁ አገልግሎቶችን በቅልጥፍና በጥራት በመስጠት ውብ፣ ፅዱና ለመኖሪያ ምቹ፣ ለኢንቨስትመንትና ለቱሪዝም ተመራጭ የሆነ ከተማ ማድረግ ነው፡፡
በዚህም ህዝቡን በማህበራዊና አኮኖሚ ልማት ሙሉ ተሳታፊና ተጠቃሚ ሊያደርጉ በሚያስችሉ ዋና ዋና ሥራዎች ትኩረት በማድረግ ሠፊ ርብርብ ተደርጎ ብዙ ሰው-ተኮር ለውጦች መጥተዋል፡፡ ልማቱና የሥራ ዕድል ፈጠራው አካታችና ዘላቂነት ያለው የከተማ ፕላንና ልማት፤ አዋጭነት፣ ግልፅነትና ተጠያቂነት ያለው የመሬት አቅርቦትና ማኔጅመንት፤ ሕብረተሰቡንና የግል ዘርፉን ያሳተፈ የቤት ልማትና አቅርቦት፤ በጥራት፣ በተመጣጣኝ ወጪና ወቅቱን የሚመጥኑ አበረታች ለውጥ ማስመዝገብ ተችሏል።
ይህም እንደ ከተማ በተወዳዳሪነት የሚሠራ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪና ማኔጅመንት አሰራርና የማስፈፀም አቅም በመገንባት የመልካም አስተዳደር መርሆዎችን ተከትሎ የተከናወና ነው፡፡ የሀዋሳ ከተማ ልዩ ሚናዋን በመለየት የኢንዱስትሪ፣ የገበያና የአገልግሎት ማዕከልነተዋን በአግባቡ ለመወጠት የሚያስችል ከአካባቢ ከተሞች እንዲሁም ገጠር ጋር በማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ካባቢያዊ ጉዳዮችን መስተጋብር በመፍጠር ተመጋጋቢና የተቀናጁ ሆነው እንዲለሙ የሚስችል እንዲሆን የተሰራ በመሆኑ ዘርፋ ብዙ ስኬቶች ማስመዝገብ ተችሏል፡፡
Mission

Vission

Values

Services
Recent News
መኩሪያ ማርሻዬ (የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ)
ሁላችሁም እንደምታውቁት በሙስሊሙ ማህበረሰብ ዘንድ አንድ ተብሎ የተጀመረው ቅዱሱ የረመዳን ወር ተጠናቆ ነገ የኢድ አል ፈጥርን በዓል ያከብራል።
የረመዳን ወር ለህዝበ ሙስሊሙ የዕዝነት፣ የመተሳሰብ፣ የመረዳዳትና ለከይር ስራ የመሽቀዳደም እና ከፈጣሪው ጋር ያለውን ቅርበት የሚያጠናክርበት ወር ሆኖ ነው የቆየው…
ከተማዋ የባህል አምባሳደር የሆነውን የኪነት ቡድን በመጠቀም ነው በሶዶ ከተማ በተለያዩ ጎዳናዎች በመዟዟር ሀዋሳን መሸጥ የሚያስችል ድንቅ ትዕይንት እውን ማድረግ የቻለችው።
የዎላይቷ ሶዶ ከተማ ነዋሪም ለከተማዋ ልዩ አድናቆት ችረዋታል።
Kuni Quchuminkera assinannihu bayriidi dodansho mito mito halaale ikkinore lainohunni xawisate geeshira
Xibbunna ontawo(150) aleenni egennantino atiletooti mereerima maaratoone beeqqate Shawwanni Hawaasira daggano.
…